SBS Amharic-logo

SBS Amharic

SBS (Australia)

SBS Radio Amharic Language Program is an independent source of news and current affairs and every week offer coverage of homeland, other international and national events

SBS Radio Amharic Language Program is an independent source of news and current affairs and every week offer coverage of homeland, other international and national events
More Information

Location:

Sydney, NSW

Description:

SBS Radio Amharic Language Program is an independent source of news and current affairs and every week offer coverage of homeland, other international and national events

Language:

Multilingual

Contact:

SBS Radio Sydney Locked Bag 028 Crows Nest NSW 1585 Australia (02) 9430 2828


Episodes

Interview with Dr Beza Abebe

3/22/2018
More
ዶ/ር ቤዛ አበበ፤ እንደምን ወደ ሕክምናው ዓለም እንደገቡ፣ የአውስትራሊያና የኢትዮጵያ የሕክምና ሙያ ተሞክሯቸውም ምን እንደሚመስል ይናገራሉ።

Duration:00:13:04

TSEHAI: 20 Years and Counting... Pt 1

3/19/2018
More
የጸሐይ አሳታሚ ድርጅት፤ ፳ ሻማዎችን ለኩሶ የሁለት አሠርት ዓመታት የሕትመት ጉዞውንና አስተዋጽዖዎቹን በምልሰት እየዘከረ ይገኛል። መጪዎቹንም ዓመታት አማትሮ በመመልከት፤ ብሩህነታቸውን ከዕሳቤው አኑሮ ውጥኖቹን እየዘረጋ ነው። የአሳታሚ ድርጅቱ መሥራችና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ወንድሙ፤ ድርጅቱ የዛሬ ፳ ዓመት እንደምን እንደቆመና ዋነኛ ተልዕኮውም ምን እንደሆነ ይናገራል።

Duration:00:26:01

Putin wins fourth term as Russian president

3/19/2018
More
የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ለአራተኛ ጊዜ ተመርጠዋል። በምርጫው ሂደት የቅርብ ተቀናቃኛቸው የነበሩት አሌክሲ ናቫልኒ እንዲገለሉ በመደረጋቸው አወዛጋቢ ሁኔታ ተፈጥሯል። የድምጽ ቆጠራው ውጤት ከቶውንም ከ2012ቱ ተጨማሪ የምርጫ ድምፆችን እንዳገኙ አመልክቷል።

Duration:00:04:14

አገርኛ ሪፖርት፤ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በአማራ ክልል በግዕዝ ፊደላት እንዲሰጥ ተጠየቀ

3/19/2018
More
አገርኛ ሪፖርት፤ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በአማራ ክልል በግዕዝ ፊደላት እንዲሰጥ ለክልሉ ፕሬዚደንት አቶ ደጉ አንዳርጋቸው ደብዳቤ መፃፋቸውን ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል።

Duration:00:09:32

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 5

3/18/2018
More
የመጀመሪያው አገር በቀል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ኋላም የኤርትራ ሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ሊቀመንበር የነበሩት ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ፤ በክፍል አምስት ቃለ ምልልሳችን የሕይወት ጉዞ ታሪካቸውን ያጠቃልላሉ። መንደርደሪያቸው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በባድመ ጦርነት መቀስቀስ ሳቢያ ‘ጦርነቱ ያለ ፓርላማና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሁንታ እንደምን ታወጀ?’ ብለው የተቃውሞ ድምጻቸውን ካሰሙት ‘የቡድን ፲፭’ አባላት እንቅስቃሴ ነው። አሰናስለውም ለኤርትራና ለኢትዮጵያ የወደፊት ዕድል መልካም ምኞት፣ ስለ ጡረታ ዘመን አኗኗር ዘይቤያቸውና ፀፀት አለብኝ ብለው ባያስቡም፤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የበደሏቸው ሰዎች ካሉ ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው በመጠየቅ ይደመድማሉ።

Duration:00:12:49

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 4

3/16/2018
More
የክፍል አራት የፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ ግለ ሕይወት ትረካ መነሻ በቀድሞው የኢሕዲሪ መንግሥትና በአማጽያን ኃይላት መካከል ተካሂደው ለስኬት ያልበቁን የአትላንታ፣ ኬንያና ሎንዶን የሰላም ድርድር ጥረቶች ናቸው። ነገን አማትረው በማየትም፤ የአሰብ ጉዳይ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ያሉ ችግሮች ሲፈቱ በድርድር አብሮ ተፈቺ ሊሆን እንደሚችል ያስባሉ።

Duration:00:20:21

አገርኛ ሪፖርት፤ የሞያሌ ተፈናቃይ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከስምንት ሺህ በላይ መድረሱ ተነገረ

3/16/2018
More
አገርኛ ሪፖርት፤ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ከቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ወደ ኬንያ የሸሹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 8592 እንደደረሰ የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር ማስታወቁን ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል። የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎቹ የኬንያን ድንበር ተሻግረው ለመጠለል ግድ የተሰኙት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥራ አስፈጻሚ ዕዝ መምሪያን ግዳጅ ለመወጣት በተሰማራ አንድ የሻለቃ ጦር አባላት የተፈጸሙት ግድያዎች በደህንነታቸው ላይ ስጋት በማሳደሩ ሳቢያ መሆኑም ተነግሯል።

Duration:00:07:39

Homelessness hitting migrants particularly hard

3/15/2018
More
የአውስትራሊያ ፌዴራል ዘውጌ ማኅበረሰባት ምክር ቤት፤ ባሕር ማዶ የተወለዱ መጤዎች ዘንድ ተከስቶ ያለው የቤት አልባነት ቁጥር መናር በጣሙን አሳስቦኛል እያለ ነው። በ2016 ይፋ በሆነው የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ አኃዝ መሠረት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አውስትራሊያን ከረገጡ መጤዎች ውስጥ 15 ፐርሰንት ያህሉ መጠለያ አልባዎች ናቸው።

Duration:00:04:17

Amara Democratic Movement Force: Tazebew Assefa

3/15/2018
More
አቶ ታዘበው አሰፋ፤ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዲኃን) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳዮችና የድርጅታቸውን ልዑካን ቡድን የአሥመራ ቆይታ አንስተው ይናገራሉ።

Duration:00:18:28

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 3

3/12/2018
More
በክፍል ሶስት የፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ ግለ ሕይወት ትረካ የሚያጠነጥነው፤ እንደምን የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ከአቋቋመው የመርማሪ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበርነት መንበራቸው ተነስተው የኤርትራ አማፂያንን ለመቀላቀል እንደበቁ ነው።

Duration:00:23:51

አገርኛ ሪፖርት፤ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ

3/12/2018
More
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የግምገማና አቅጣጫ ቅየሳ ስብሰባ ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል።

Duration:00:07:59

What Does The Future Hold For Ethiopia?

3/11/2018
More
አቶ ጀማል ድሬ ከህሊፍ፤የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፤ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን ከወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው፤ እንዲሁም፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንድምታ አንስተው ይናገራሉ።

Duration:00:15:19

Community Building: Wondemagegnehu Addis and Zerihun Gizaw

3/11/2018
More
የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር በጅሮንድ፤ ማኅበሩ መጋቢት ፱ ማርች 18 ስለ ጠራው አጠቃላይ ስብሰባ አጀንዳ ይናገራሉ።

Duration:00:18:37

Sworn Duty: Journalist Eskinder Nega – Pt 2

3/11/2018
More
የበርካታ የንግግር ነፃነት ሽልማቶች ተሸላሚው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ያለውን ፅኑ ዕ አቋምና እምነት ይገልጣል። በእሥር ጊዜያቱ ድጋፋቸውን ለቸሩት ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላትም ምሥጋናውን ያቀርባል።

Duration:00:16:44

Interview with Journalist Mariamawit Elias Koslay

3/9/2018
More
ጋዜጠኛ ማርያማዊት ኤልያስ ኮስላይ ጋር እንደምን ወደ ሙያው ተስባ እንደዘለቀችና ስለ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሚና ትናገራለች።

Duration:00:13:36

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 2

3/9/2018
More
ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ፤ በክፍል ሁለት የግለ ሕይወት ትረካቸው የዓይን ምስክርና ተሳታፊ የነበሩባቸውን ሁለት አንኳር የታሪክ ምዕራፎችን ያነሳሉ። የ1953ቱን የታህሳስ ‘ግርግር’ እና የየካቲት ‘66ቱን የአብዮት ‘ፍንዳታ’ ታሪካዊ ክስተቶች።

Duration:00:20:49

አገርኛ ሪፖርት፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት

3/9/2018
More
አገርኛ ሪፖርት፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን የኢትዮጵያ ጉብኝት ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል።

Duration:00:09:02

Sworn Duty: Journalist Eskinder Nega – Pt 1

3/8/2018
More
የበርካታ የንግግር ነፃነት ሽልማቶች ተሸላሚው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በሽብር ክስ እንደምን የ፲፰ ዓመታት እሥር ተበይኖበት ዘብጥያ እንደወረደና ከስድስት ዓመታት ተኩል የእሥራት ጊዜያት በኋላ እንደተለቀቀ ይናገራል። ለስምንት ጊዜያት በተደጋጋሚ ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር፤ የእሥር ጊዜያቱ ‘እምነትና ዲሞክራሲ’ ፅኑዕ የሕይወቱ ማዕከል እንዲሆኑ ጉልህ ሚና ማሳደራቸውን ይገልጣል።

Duration:00:15:17

Settlement Guide: How to get an apprenticeship in Australia

3/7/2018
More
የሥራ መደብ ስልጠና፤ ለወጣት መጤዎች ወደሚሹት የሥራ ዘርፍ ለመዝለቅ አንዱ ማለፊያ መንገድ ነው። የሥራ መደብ ስልጠና የክፍያ ሥራን ከልምምድ ጊዜያት ጋር ያጣመረ ነው። በሙሉ ወይም በግማሽ ቀናት ሰልጣኝነት፤ አሊያም ትምህርት ቤት ሳሉ መከወን ይቻላል።

Duration:00:05:22

Housing report blames state, federal governments for problem

3/5/2018
More
አዲስ ይፋ የሆነ የምርምር ግኝት አውስትራሊያ ውስጥ ተከስቶ ላለው ከአቅም በላይ ለሆነ የቤት ዋጋ ቀውስ ተጠያቂነቱን በክፍለ አገራትና የፌዴራል መንግሥታቱ ላይ ጥሏል። ሰበቡንም፤ አስተውሎት የጎደለው የዕቅድ ነደፋ ብሎታል። የግራታን ኢንስቲትዮት የምርምር ማዕከል የመሪዎቹ እርምጃዎች ከቶውንም ችግሩን እንዳባባሰው ጠቁሟል። በመፍትሔነትም ወደ አውስትራሊያ የሚዘልቁ የመጤዎችን ቁጥር መቀነስ የመጨረሻ እርምጃ ሊሆን ይገባል ሲል ምክረ ሃሳቡን ለግሷል።

Duration:00:02:52

Try Premium for 30 days

Live games for all NFL, MLB, NBA, & NHL teams
Commercial-Free Music
No Display Ads