
SBS Amharic
SBS (Australia)
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Location:
Sydney, NSW
Genres:
News & Politics Podcasts
Networks:
SBS (Australia)
Description:
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Language:
Multilingual
Contact:
SBS Radio Sydney Locked Bag 028 Crows Nest NSW 1585 Australia (02) 9430 2828
Episodes
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ ታዳጊ ወጣት አውስትራሊያውያን በጋውን ያለ ማኅበራዊ ሚዲያ በደስታ እንዲያሳልፉ አሳሰቡ
12/9/2025
ፕሬዚደንት ዜለንስኪ የዩክሬይንን ድንበር ለመለወጥ ሕጋዊም ሆነ የሞራል መብት እንደሌላቸው ገለጡ
Duration:00:07:22
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 እንዲሆን ቀን ተቆረጠ
12/9/2025
የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚያችል ክትባት በደቡብ ኢትዮጵያና በሲዳማ ክልል በተመረጡ አካባቢዎች ለፈቃደኛ ግለሰቦች መሰጠት ተጀመረ
Duration:00:08:34
"ሼክስፒር እኔ ኮርዴሊያን ሆኜ ስጫወት ቢያየኝ፤ እርግጠኛ ነኝ፤ ጥቁር ሴት በመሆኔ ይደነግጣል። በእሱ ጊዜ ዘረኛነት በጣም ነበር።" ተዋናይት አሁንም አበበ
12/9/2025
ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ በትወና ላይ ያለውና ጃኑዋሪ 4 የሚያከትመው የሼክስፒር King Lear ተውኔት ኮርዴሊያን ብቻ አይደለችም። ተውኔት ባሻገር ስላላት የማኅበራዊ ፍትሕና የተፈጥሮ ክብካቤ አንቂነ ሕይወቷ፣ የሼክስፒር ተውኔቶች ዘመን ተሻጋሪነትና አሁንም ድረስ ገነን ሆኖ የቆየበትን አስባብ አንስታ አተያይዋን ታጋራለች።
Duration:00:23:30
"ወጣት ሴቶች ውስጣቸው ጥንካሬና ችሎታ እንዲኖራቸው ነው የምፈልገው፤ ለውጥ ቢኖርም አሁንም ወንዶችና ሴቶች ገና እኩል አይደሉም" ተዋናይት አሁንም አበበ
12/8/2025
ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ጃኑዋሪ 4 ለማብቃት መድረክ ላይ ለቲአትር አፍቃሪዎች እየተተወነ ባለው የሼክስፒር King Lear ተውኔት የኮርዴሊያን ገፀባሕሪ ተላብሳ በመተወን ላይ ናት። ከስሟ ስያሜ እስከ ተውኔት ሕይወቷ ታወጋለች። አውስትራሊያ ተወልዳ ብታድግም፤ አማርኛዋ የጠራ ነው።
Duration:00:23:22
የቀድሞው የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የዋን ኔሽን ፓርቲን ተቀላቀሉ
12/7/2025
በኒው ሳውዝ ዌይልስ የእሳት ቃጠሎ ሳቢያ የአንድ እሳት አደጋ ተከላካይ ሕይወት አለፈ
Duration:00:05:45
ኢትዮጵያ በእዚህ ሳምንት የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው
12/7/2025
የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ለመሳተፍ የድጋፍ ፊርማ እንዲያቀርቡ የሚደነግገው አዋጅ ታገደ
Duration:00:11:02
የቪክቶሪያ መንግሥት ከአንድ ሺህ በላይ የመንግስት ሠራተኞችን ሊቀንስ ነው
12/4/2025
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ በ2025 ያደመጧቸውን ዋነኛ ዘፋኞችና ባንድ ይፋ አደረጉ
Duration:00:02:57
ዶናል ትራምፕ የሩስያና ዩክሬይን ጦርነትን ለማክሰም ተቃርቤያለሁ ሲሉ፤ በጦርነት ላይ ያሉት ሃገራት እርግጠኞች አይደሉም
12/3/2025
ዩቱዩብ - አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የጣለችውን የማኅበራዊ ሚዲያ ዕቀባ ግብር ላይ አውላለሁ አለ
Duration:00:05:54
በአዲስ አበባ የHIV / AIDS ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ይገኛል ተባለ
12/2/2025
በኢትዮጵያ ያሉ ብሔራዊ ፓርኮች ሰፊ የመሠረተ ልማት ክፍተት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
Duration:00:09:02
"ዕድሜ ልክ እየለመን መኖር የለብንም። የእኛ ሕዝብ አስተዋፅዖ ማድረግ አለበት፤ እንደ ሕዝብ ክብራችንም ይጨምራል" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
12/2/2025
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና ማኅበራትን አስፈላጊ ሁነኛ ሚናዎች ነቅሰው ያመላክታሉ።
Duration:00:46:02
"በኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዘንድ ትልቁ ተግዳሮት አዳዲስ አመራሮችን ለመምረጥ ተተኪዎችን አለማግኘት ነው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
12/2/2025
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና ማኅበራት ግንኙነቶችን አስመልክተው ይናገራሉ።
Duration:00:26:16
ከሶስት ሀገራት ጋር ፍርደኞችን ለማስተላለፍና አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችሉ ስምምነቶች ይሁንታ እንዲያገኙ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ
11/30/2025
ድንቅነሽ (ሉሲ) በኖረችበት ዘመን እንደኖረ የተገመተ የ3.4 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ ተገኘ
Duration:00:13:43
"ዓይኔ እግዚአብሔር የሰጠኝ ትልቁ ስጦታዬ አንቺ ነሽ እላት ነበር" የወ/ሮ ዓይንዋጋ አስናቀ ባለቤት ዶ/ር ተክቶ ካሣው
11/27/2025
በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩትን የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ ዓይንዋጋ አስናቀ ትኩ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ ባለቤታቸው ዶ/ር ተክቶ ካሣው፣ እህት ድርብ አስናቀ፣ የቅርብ የቤተሰብ ወዳጆች ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ፣ ዶ/ር ማማሩ አየነውና ዶ/ር አዳነ ዳምጠው ዓይንዋጋን በክብር ይዘክራሉ፤ ትውስታዎቻቸውን ያጋራሉ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ቅዳሜ ኅዳር 20 / ኖቬምበር 29 ከቀኑ 7 ሰዓት (1:00 pm) Springvale Botanical Cemetery ይፈፀማል።
Duration:00:38:08
#100 More or less? Talking about quantities - #100 ይነስ ወይም ይብዛ? ስለ መጠን መናገር
11/26/2025
Learn how to talk about amounts and quantities in everyday English. - ስለ ብዛትና ስፍር አዘቦታዊ የእንግሊዝኛ አነጋገርን ይማሩ።
Duration:00:07:33
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ማካሔጃ 10 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስታወቀ
11/25/2025
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ 'ስምንት ስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ይዞታ ለማዞር ያደረግኩት ጥረት ባለ ሃብቶች ፍላጎት ባለማሳየታቸው አልተሳካም' አለ
Duration:00:08:49
"የኢትዮጵያ አየር መንገድን 'ከአፍሪካ የወጣ አፍሪካዊ አየር መንገድ' ነበር የምንለው፤ አሁን 'ከአፍሪካ የወጣ የዓለም አየር መንገድ' ነው የምንለው" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ
11/25/2025
"አውስትራሊያ ጥሩ ሀገር ናት፣ ብንመጣም የምናተርፍባት እንጂ የምታከስረን ሀገር አይደለችም፤ ሕዝቧም ተቀባይ የሆነ ሀገር ስለሆነች ወደ አውስትራሊያ መብረር የማይፈልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የለም። እርግጠኛ ነኝ፤ አውሮፕላን እንደተገኘ የድርጅቴ ቀዳሚ ጉዳይ የሚሆነው ወደ አውስትራሊያ መብረር ነው" ያሉት ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ፤ ተሰናባች የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላናድ ቀጣና ሥራ አስኪያጅ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የቀጣና ተግዳሮቶችንና ስኬታማ ክንውኖችን አንስተው ይናገራሉ።
Duration:00:29:40
የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበራትን በባሕር ማዶ የማቋቋም ፋይዳ፣ ሳቢና ገፊ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
11/25/2025
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የማኅበረሰብ ማኅበራትን የአገልግሎት ፋይዳዎች ያስረዳሉ።
Duration:00:30:31
በአዲስ አበባ በፆታዊ ጥቃት የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሚሔዱት መካከል ከ70-80 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች መሆናቸው ተገለጠ
11/24/2025
ከ44 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሁንም የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት የላቸውም ተባለ
Duration:00:13:01
"የሥራ አጥነትና የወጣት ጥፋተኞች እሥራት ቁጥር መናር ምክንያት አንዱ መንስኤ ዘረኛነት ነው ብዬ አስባለሁ" ዶ/ር ይርጋ ገላው
11/19/2025
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብ ዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ ስለ ወጣት አፍሪካውያን ሥራ አጥነት ቁጥርና ማኅበራዊ ተግዳሮት አስባቦች ይናገራሉ።
Duration:00:30:04
"ኢትዮጵያውያንም ማንኛውም ጥቁር የሚደርስበት ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ጥቁር አይደለሁም የሚል አስተሳሰብ ካለ ይህ የንቃት ጉድለት ነው፤ ያሳስባል" ዶ/ር ተበጀ ሞላ
11/19/2025
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብ ዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አክሎ በፍልሰተኞች ዘንድ ያሉ የማንነት አተያዮችን ያጋራሉ።
Duration:00:20:10