
SBS Amharic
SBS (Australia)
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Location:
Sydney, NSW
Genres:
News & Politics Podcasts
Networks:
SBS (Australia)
Description:
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Language:
Multilingual
Contact:
SBS Radio Sydney Locked Bag 028 Crows Nest NSW 1585 Australia (02) 9430 2828
Episodes
አዲስ አበባ እንጦጦ ላይ የሚገኙትን የባሕር ዛፎች በሶስት ዓመታት ውስጥ በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ዕቅድ መያዟን አስታወቀች
7/6/2025
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስጋትን፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬንና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈፅመዋል ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ አዲስ የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ
Duration:00:15:00
ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌና ሬስቶራንት ከሜልበርን - አውስትራሊያ 15 ምርጥ ካፌዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ
7/4/2025
አቶ ዳንኤል አለማር፤ የጎጆ ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት የቡናና ምግብ አቅርቦታቸው ለሽልማት የመጨረሻ ማጣሪያ ከቀረቡት 15 የሜልበር ምርጥ ካፌዎች አንዱ ለመሆን በመብቃቱ "የሬስቶራንቴ ስም 'ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌ እና ሬስቶራንት'፤ ሀገርን ተሸክሞ ያለ ትልቅ ስም ያለው ነው። ሀገሬን በማስጠራቴ ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል" ሲሉ፤ እህታቸውና ሥራ አስኪያጅ መሠረት አለማር ፤ ሕልማቸው በዕጩነት ከ15 ምርጥ የሜልበርን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ አንዱ ለመሆን በመብቃት እንደማይገታ ይናገራሉ።
Duration:00:18:11
"ጠቅላላ ጉባኤ የጠራነው የፋይናንስ ሪፖርት ለማቅረብ፤ ለአሁኑና ወደፊትም ለሚመጣው ማኅበረሰብ የሚጠቅም የመተዳደሪያ ደንብ ክለሳ ላይ ለመነጋገር ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
7/3/2025
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለሰኔ 29 / ጁላይ 6 በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለመላ የማኅበረስብ አባላት ስለቀረበው የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪና የመነጋገሪያ ዋነኛ አጀንዳዎች ያስረዳሉ።
Duration:00:23:52
ሃማስ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ "የመጨረሻ" የተኩስ አቁም ውል ብለው ያቀረቡትን ዕሳቤ እንደሚያጤነው አስታወቀ
7/2/2025
የኢራን ፕሬዚደንት ኢራን ለዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጄንሲ ትብብሯን እንድትነፍግ የሚፈቅድ ሕግ አፀደቁ
Duration:00:03:30
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እሥራኤል ለ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ይሁንታዋን መቸሯን ገለጡ
7/2/2025
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ የአራትዮሹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ፍሬያማ ነበር አሉ
Duration:00:07:28
የሕገ መንግሥት ጥሰት ጥያቄ አስነስቶ የነበረው የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለቤትነት ረቂቅ አዋጅ በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ተቀይሮ ፀደቀ
7/1/2025
የሕወሓትን ክፍፍል ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመሩ ነው የሚል ስጋት ተፈጥሯል ተባለ
Duration:00:12:59
"ፕሮፌሰሮቹ - መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ፕሮፌሰሮች ያለፉበትን ሕይወት፣ ለሀገሪቱ ያላቸው ከፍተኛ ሚናና የኢትዮጵያን የታሪክ ገፅታ ለማሳየት የተፃፈ ነው" ተሾመ ብርሃኑ
7/1/2025
ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ አዲስ ለሕትመት ያበቁት "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ስለምን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ሙያዊ አስተዋፅዖዎች ላይ ለማተኮር እንደወደዱ ይናገራሉ።
Duration:00:19:21
"መጽሐፉን መፃፉ እንደመስታወት በለሰለሰ አለት ላይ የመውጣት ያህል ነው" ደራሲ ብርሃኑ ተሾመ ከማል
7/1/2025
በሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው 32 መፃሕፍትንና ከ2000 በላይ መጣጥፎችን ለአንባቢያን ያበረከቱት አንጋፋ ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ ሰሞነኛ ስለሆነው "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ተልዕኮና ይዘት ያስረዳሉ።
Duration:00:13:57
"ያስመረቅነው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ለአማኞች አምልኮ ብቻ ሳይሆን ለማኅበረሰቡም ጭምር ነው" ፓስተር ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ
6/29/2025
"በቤተ ክርስቲያንም ተከፋፍለን፣ በማኅበረሰብም ተከፋፍለን፣ በዘርም ተከፋፍለን ያሳለፍናቸው ምንም አልጠቀሙንም። አንድ ከሆንን፤ ከተባበርን፤ ከእዚህ በላይ መሥራት እንችላለን። ኅብረት የውስጥም የውጭም ጩኸቴ ነው!" አቶ ዳንኤል አለማር፤ በሜልበርን የዘፀዓት ኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ኅብረት አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ
Duration:00:15:26
የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ለውጭ ባንኮችና ሙዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች በይፋ መከፈቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
6/29/2025
ኢትዮጵያን ጨምሮ 39 ሀገራት በግጭቶችና አለመረጋጋቶች ምክንያት የከፋ ረሃብና ድህነት ማዕከል እየሆኑ ስለመሆናቸው የዓለም ባንክ ባወጣው ይፋ ሪፖርት አመላከተ
Duration:00:13:58
ዶናልድ ትራምፕ የኢራንና እሥራኤል ጦርነት ከእነአካቴው ማክተሙን ዳግም ሲያስታውቁ፤ የኢራን ፓርላማ የሀገሪቱ ኑክሊየር ፕሮግራም ተፋጥኖ እንዲቀጥል በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳለፈ
6/26/2025
ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በሚቀጥለው ሳምንት የቀጥታ ሁለትዮሽ ውይይት ሊጀምሩ ነው
Duration:00:04:52
ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ከሕግና መመሪያ ውጪ የተጠቀሙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እስካሁን የገንዘቡን 86 በመቶ አለመመለሳቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
6/24/2025
አማኑኤል የአዕምሮ ልዩ ሆስፒታል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ተገልጋዮች የሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ገለጠ
Duration:00:09:53
የዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት ያሰራውን ህንጻ ቤ/ክ በመጪው ቅዳሜ ሊያስመርቅ ነው
6/24/2025
አቶ ዳንኤል አለማር ከዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት የህንጻ አሰሪ ሰብሳቢ ፤ በሜልበርን ከተማ በመጪው ቅድሚ የሚመረቀው የቤተክርስቲያን ህንጻ ፤ ህብረተሰቡ ከሌለው አቅሙ ቀንሦ ለትውልዱ እና ለመጪው ትውልድ ያሳነጸው ሲሆን ፡ በህንጻ አሰሪው ኮሚቴው ስም ምስጋናዪን አቀርባለሁ ብለዋል ። አያይዘውም በምርቃቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
Duration:00:11:19
ፕሬዚደንት ትራምፕ ኢራንና እሥራኤል ለተኩስ አቁም ተስማምተዋል ማለታቸውን ኢራን አስተባበለች፤ ከእሥራኤል በኩል ይፋዊ ምላሽ እየተጠበቀ ነው
6/24/2025
የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን "ኢራን ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ማድረግ ካስፈለገ በኢራን ሕዝብ እንጂ በቦምብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን የሥርዓት ለውጥ ዕሳቤ ተቹ
Duration:00:03:52
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍን ከሰኔ 24 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ልታደርግ ነው
6/22/2025
በሳዑዲ ዓረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ 37 ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል
Duration:00:13:50
ኢራን ባደረሰችው የሚሳይል ጥቃት የደቡባዊ እሥራኤል ሶሮካ ሆስፒታል ጉዳት ደረሰበት
6/19/2025
በሺህዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን ኢራንና እሥራኤልን ለቅቀው ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ ተመዝግበዋል
Duration:00:05:49
የኢራን መሪ ኢራን ለእሥራኤል ምሕረት አታደርግም ሲሉ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት በፊናቸው ኢራን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ‘እጇን እንድትሰጥ’ አሉ
6/18/2025
አውስትራሊያ በሩስያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጣለች
Duration:00:08:16
በአዲስ አበባና ስድስት ክልልሎች የተስፋፍው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እስካሁን 22 ሰዎችን አጥቅቷል
6/17/2025
በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ በማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን የሚመረምሩ አካላት አስገዳጅ ሆኖ ሲገኝ ከግድያ በስተቀር ያሉ የምርመራ መንገዶችን የሚፈቅደውና አነጋጋሪ የሆነው አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ
Duration:00:08:37
#88 Celebrating an anniversary (Med) - #88 Celebrating an anniversary (Med)
6/16/2025
Learn how to congratulate someone on their work or wedding anniversary. - Learn how to congratulate someone on their work or wedding anniversary.
Duration:00:15:47
በአዲስ አበባ በቀን በትንሹ አራት ሕፃናት በወላጆቻቸው መንገድ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ ተመለከተ
6/15/2025
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት አሜሪካ እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር አስታወቁ
Duration:00:13:36