
SBS Amharic
SBS (Australia)
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Location:
Sydney, NSW
Genres:
News & Politics Podcasts
Networks:
SBS (Australia)
Description:
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Language:
Multilingual
Contact:
SBS Radio Sydney Locked Bag 028 Crows Nest NSW 1585 Australia (02) 9430 2828
Episodes
ፕሬዚደንት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ እንዳደረገ የተጠረጠረው ግለሰብ ማምሻውን ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
4/27/2026
የደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ለቅቀው እየወጡ ነው
Duration:00:03:58
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ እንዲያከናውኑ ከተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 22ቱ ሕገወጥ ድርጊት በመፈፀማቸው መዝጋቱን አስታወቀ
4/27/2026
የፌዴራል ፖሊስ በቴዲ አፍሮ ጉዳይ ምላሽ ሰጠ፤ የድምፃዊው የቅርብ ወዳጆች የፖሊስን ምላሽ በትክክለኛ መረጃነት አልተቀበሉም
Duration:00:10:18
መብቶቻቸውን ለነፈገቻቸው ሀገር መዋጋት፤ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የጦር አባላት አገልግሎት ዝክረ መታሰቢያ
4/24/2026
ከአንደኛው የዓለም ጦርነት አንስቶ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በአውስትራሊያ የመከላከያ ሠራዊት አባልነት አገልግለዋል። ብሔራዊ የዜግነት መብት አልነበራቸውም። ሆኖም ግና ዜግነት የነፈገቻቸው ሀገር በመቶዎች የሚቆጠሩቱን ለወታደራዊ ግዳጅ ባሕር አሻግራ ልካለች።
Duration:00:06:35
"የሐበሻ ማኅበረሰብ መጥቶ ቢያየኝ፤ ቢደግፈኝ ደስ ይለኛል። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ነገር የሚያገኝበት ትዕይንት ነው" ሶሊያና እርሴ
4/22/2026
ሶሊያና እርሴ፤ ትንፋሽ አስዋጭ፣ የልብ ትርታን ደላቂ፣ ከዮጋም፣ ከጂምናስቲክም ልዩ አካላዊ እጥፋትና ዝርጋታን ልዩ ምትሃት መሰል ክህሎት ግድ የሚለው፤ ግና ሞገስን ተላብሶ መድረክ ላይ ግዘፍ የሚነሳ Contortionist Extraordinaire ኢትዮጵያዊት ናት። ድንቅ ክህሎቷም ከኤፕሪል 7 እስከ ሜይ 24 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከClub Kabarett ጋር ለሕዝብ ዕይታ ይቀርባል። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎቿ እንዲሆኑ ትጋብዛለች።
Duration:00:08:32
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን-እሥራኤል-ዩናይትድ ስቴትስ ተኩስ አቁምን ላልተወሰነ ጊዜ አራዘሙ
4/22/2026
የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ናፍጣ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ
Duration:00:04:06
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ድረስ 47 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች መመዝገባቸውን አስታወቀ
4/21/2026
የኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምግብነት እየዋለ መሆኑ ተነገረ
Duration:00:05:36
ዩናይድ ስቴትስ የኢራንን መርከብ በቁጥጥሯ ስር አዋለች፤ ኢራን የአፀፋ እርምጃ እወስዳለሁ አለች
4/20/2026
የዋን ኔሽን የሕዝብ አስተያየት ድጋፍ መውረድ ጀመረ፤ ሆኖም ከፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ ቀድሞ ሔዷል
Duration:00:04:25
የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን "ቴዲ አፍሮ" ኢቶሪካ አልበም ሬኮርዶችን መስበሩን ቀጥሏል
4/20/2026
ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይቶች በሀገር ውስጥ ለመገጣጠምና መሞከር የሚያስችላትን ግዙፍ የማዕከል ግንባታ ከሩስያ የጠፈር ተቋም ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅቷን ማጠናቀቋ ተነገረ
Duration:00:11:00
"የሴቶች ጉዳይ የተወሰኑ ሰዎች ኃላፊነት ብቻ አይደለም። ሁላችንም ለሴቶች ክብር፣ ነፃነት፣ እኩልነትና በዋናነት ለደህንነታቸው መቆም አለብን።" ናዲያ ሞናያ
4/17/2026
በሥርዓተ ትምህርት፣ የሴቶችና መድብለ ባሕል ተኮር የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ምርምራቸውን በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ እያካሔዱ ያሉት ወ/ት ናዲያ ሞናያ፤ ከፊል የምርምር ግኝቶቻቸውንና ፖሊሲ ነክ ጉዳዮችን አንስተው ያስረዳሉ።
Duration:00:10:26
"ግጥም ውስጤ ያለውን ስሜት የምገልፅበት፣ አንባቢን በእኔ ዓለም ውስጥ፣ ስሜቶቼ ውስጥ የምጋብዝበት መድረክ ነው" ናዲያ ሞናያ
4/17/2026
በዩኒቨርሲቲ Exeter የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናዲያ ሞናያ፤ ምርምራቸው ስለሚያተኩርበት ለውጥ የሚያሻቸው የሴቶች ጉዳዮችና የመድብለ ባሕል ፋይዳዎችን አንስተው ያናገራሉ። ከግጥም ሥራዎቻቸው በቅርቡ "I Hugged a Tree" በሚል ርዕስ ለአባታቸው ዝክረ መታሰቢያ ከፃፉት የስንኝ ቋጠሯቸው በቅንጭቡ ያስደምጣሉ።
Duration:00:25:36
"ከመማር ጋር ኃላፊነት አለ፤ የተማሩትን ለሌላው ማስተላለፍ የራስን ኃላፊነት መወጣት ነው። ለሕይወትም ትርጉም አለው።" ናዲያ ሞናያ
4/16/2026
ናዲያ ሞናያ - በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናቸው። ውልደትና ዕድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የኢትዮጵያዊት፣ ኤርትራዊትና ጣሊያናዊት ዝንቅ ብሔራዊ ማንነትን አጣምረው ይዘዋል። ሁለት ሀገርኛና አምስት የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ተናጋሪ ናቸው። የውልደት፣ ዕድገትና የትምህርት ሕይወታቸውን ነቅሰው ያጋራሉ።
Duration:00:19:00
በአውስትራሊያ ጅሎንግ በሚገኝው የነዳጅ ማጣሪያ የእሳት አደጋ ተከሰት
4/16/2026
የአውስትራሊያ ከተሞች የራሳቸውን የነዳጅ ክምችት ለርመፍጠር ቅድመ ዝግጅት ጀምረናል አሉ
Duration:00:04:40
Women’s legal services in Australia: Understanding your options - በአውስትራሊያ ለሴቶች ነጻ የህግ አገልግሎት ተቋማት አማራጮች እንዳሉ ይረዱ
4/15/2026
Workplace discrimination, gender-based violence and financial inequality—these are just some of the reasons why women need dedicated legal services. You don’t have to navigate the legal system alone. In Australia, free legal services exist to advocate for vulnerable women in ways that are safe, confidential and culturally appropriate. - ሴቶች የተለየ የህግ ባለሙያዎች እንዲያስፈልጋቸው ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል ፤ በስራ ቦታ የሚፈጸም መድልዎ ፤ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ፤ በገቢ ላይ የሚደረግ ማበላለጥ የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው ፡፡ በአውስትራሊያ የህግ ተቋማትን ብቻዎትን ማፈላልገ አይጠበቅብዎትም ፡፡ በችግር ላይ ያሉ ሴቶች ደህንነታቸ በተጠበቀ ሁኔታ ፤ ምስጢራቸው እና ባህላቸውን ባገናዘበ መልኩ ነጻ የህግ አገልግሎት አለ፡፡
Duration:00:10:29
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ቀውስ በጦርነት አይፈታም ፤ መፍትሄው የሰላም ውይይት ነው - አንቶኒዮ ጉተሬዝ
4/15/2026
በሱዳን ከ 21 ሚልዮን በላይ ዜጎች ለጽኑ ረሀብ እና የምግብ እጦት ተጋልጠዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ወኪል አስታወቁ
Duration:00:07:32
አገርኛ ሪፓርት - በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች መሰርታዊ አቅርቦት ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ገንዘብ ያስፈልጋል ተባለ
4/14/2026
በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ከደቡብ ሱዳን ፤ ኬንያ ኤርትራ እና ሶማሊያ የተፈናቀሉ ስደተኞች እንደሚኖሩ ተገለጸ
Duration:00:09:02
በሺህ የሚቆጠሩ አራናውያን አሜሪካ በሆርሙዝ የጣለችውን ገደብ በቃወም ለሰልፍ ወጡ
4/13/2026
የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የኡበር አሽከርካሪዎች ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ ዋጋ እንዲያስከፍሉ ደንብ ወጣ
Duration:00:04:53
"ይህ የትንሣኤ በዓል ለሁላችንም የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመሰባሰቢያ፣ ራሳችንን የመጠየቂያ በዓል እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን" ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ
4/11/2026
መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የበዓለ ትንሣኤን ትርጓሜ ያስረዳሉ። የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Duration:00:14:02
"እንኳን ለበዓለ ትንሣኤ አደረሳችሁ! እግዚአብሔር ሀገራችንን ኢትዮጵያንና መኖሪያችንን አውስትራሊያን ይባርክ" ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ
4/11/2026
ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ፤ በዘፀዓት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አገልጋይ፤ የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የ ‘እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን’ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Duration:00:06:09
"የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብን ሁለቱንም ወላጆች ላጡ ተፈናቃይ ልጆች ላደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦ እናመሰግናለን" ወ/ሮ ገነት ቤተ ጌራወርቅ የም/ቤት አባል
4/10/2026
ወ/ሮ ገነት ቤተ ጌራወርቅ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ የኤፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በደብረ ብርሃን መጠለያ ቻይና ካምፕ ተጠላይ እናት ሩቂያ አሕመድ ስለ ተፈናቃዮች ሕይወት፣ በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አስተባባሪነት ሁለት ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት ስለተደረገላቸው ሰብዓዊ እርዳታ አንስተው ይናገራሉ። ልባዊ ምስጋናቸውንም ያቀርባሉ።
Duration:00:17:01
ለጋሽ እጆች ከደቡብ አውስትራሊያ እስከ ደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች
4/10/2026
የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ለገሰ ጋረደው፣ የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት አቶ ጥላዬ ተከተልና አቶ መሐመድ በያን፤ እንደምን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ከወለጋ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ልገሳቸውን እንደቸሩ ይናገራሉ።
Duration:00:25:05