SBS Amharic-logo

SBS Amharic

SBS (Australia)

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Location:

Sydney, NSW

Description:

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Language:

Multilingual

Contact:

SBS Radio Sydney Locked Bag 028 Crows Nest NSW 1585 Australia (02) 9430 2828


Episodes
Ask host to enable sharing for playback control

The overlooked story: Aboriginal and Torres Strait Islander service on ANZAC Day - ወደ ጎን የተገፋውታሪክ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴተኞች አገልግሎት በአንዛክ ቀን

4/30/2026
Each year Australians gather on ANZAC Day to remember those who served in wars, conflicts and peacekeeping missions. But whose stories are we remembering? Are there stories we don’t always hear? In this episode we explore an important part of Australia’s history that has often been overlooked—the service of Aboriginal and Torres Strait Islander peoples. - በየዓመቱ አውስትራሊያውያን የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ጦር ሠራዊት ኮር ቀን (አንዛክ ቀን) ለማክበር ይታደማሉ። እኒያን በጦርነቶች፣ ግጭቶች እና የሰላም አስከባሪ ግዳጆች ተሰማርተው አገልግሎቶቻቸውን አበርክተው የነበሩትን በክብር ለመዘከር። ይሁንና የምንዘክረው የእነ ማንን ታሪክ ነው? አዘውትረን የማንሰማቸው ታሪኮችስ አሉ? በእዚህ ክፍለ ዝግጅት በጣም ጠቃሚ የሆነ ግና ቸል የተባለ ታሪክን እናነሳለን፤ የአቦርጂናልና ቶረስ ሰርጥ ደሴት ሰዎችን አገልግሎት።

Duration:00:07:50

Ask host to enable sharing for playback control

#109 Talking about ageing parents (Med) - #109 ዕድሜያቸው እየገፋ ስላሉ ወላጆች መናገር

4/29/2026
Learn English useful for talking about ageing parents and family responsibilities. Practise everyday phrases for describing challenges, offering help, and discussing how to support parents. - ዕድሜያቸው እየገፋ ስላሉ ወላጆችና የቤተሰብ ኃላፊነቶች ለመናገር እንግሊዝኛን መማር ጠቀሜታ አለው። በየዕለቱ ተግዳሮቶችን፣ እርዳታ ልገሳንና ወላጆችን እንደምን ማገዝ እንደሚቻል ገላጭ የሆኑ አባባሎችን ይለማመዱ።

Duration:00:09:25

Ask host to enable sharing for playback control

በኢትዮጵያ በቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሠራተኞችና ኃላፊዎችን በፅኑዕ እሥራት የሚቀጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

4/29/2026
የትምህርት ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከሁሉም ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

Duration:00:09:16

Ask host to enable sharing for playback control

የፖርት ኧርተር የጅምላ ግድያ 30ኛ ዓመት ዝክረ መታሰቢያ ተከናወነ

4/28/2026
በአውስትራሊያ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን የቪክቶሪያ ክፍለ ሃገር የሌበር መንግሥት የአዋቂና ወጣት ወንዶች ሚኒስትር መሾምን ተከትሎ፤ የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ የአዋቂና ወጣት ወንዶች ልዑክ ሰየመ

Duration:00:04:40

Ask host to enable sharing for playback control

ፕሬዚደንት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ እንዳደረገ የተጠረጠረው ግለሰብ ማምሻውን ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው

4/27/2026
የደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ለቅቀው እየወጡ ነው

Duration:00:03:58

Ask host to enable sharing for playback control

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ እንዲያከናውኑ ከተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 22ቱ ሕገወጥ ድርጊት በመፈፀማቸው መዝጋቱን አስታወቀ

4/27/2026
የፌዴራል ፖሊስ በቴዲ አፍሮ ጉዳይ ምላሽ ሰጠ፤ የድምፃዊው የቅርብ ወዳጆች የፖሊስን ምላሽ በትክክለኛ መረጃነት አልተቀበሉም

Duration:00:10:18

Ask host to enable sharing for playback control

መብቶቻቸውን ለነፈገቻቸው ሀገር መዋጋት፤ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የጦር አባላት አገልግሎት ዝክረ መታሰቢያ

4/24/2026
ከአንደኛው የዓለም ጦርነት አንስቶ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በአውስትራሊያ የመከላከያ ሠራዊት አባልነት አገልግለዋል። ብሔራዊ የዜግነት መብት አልነበራቸውም። ሆኖም ግና ዜግነት የነፈገቻቸው ሀገር በመቶዎች የሚቆጠሩቱን ለወታደራዊ ግዳጅ ባሕር አሻግራ ልካለች።

Duration:00:06:35

Ask host to enable sharing for playback control

"የሐበሻ ማኅበረሰብ መጥቶ ቢያየኝ፤ ቢደግፈኝ ደስ ይለኛል። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ነገር የሚያገኝበት ትዕይንት ነው" ሶሊያና እርሴ

4/22/2026
ሶሊያና እርሴ፤ ትንፋሽ አስዋጭ፣ የልብ ትርታን ደላቂ፣ ከዮጋም፣ ከጂምናስቲክም ልዩ አካላዊ እጥፋትና ዝርጋታን ልዩ ምትሃት መሰል ክህሎት ግድ የሚለው፤ ግና ሞገስን ተላብሶ መድረክ ላይ ግዘፍ የሚነሳ Contortionist Extraordinaire ኢትዮጵያዊት ናት። ድንቅ ክህሎቷም ከኤፕሪል 7 እስከ ሜይ 24 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከClub Kabarett ጋር ለሕዝብ ዕይታ ይቀርባል። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎቿ እንዲሆኑ ትጋብዛለች።

Duration:00:08:32

Ask host to enable sharing for playback control

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን-እሥራኤል-ዩናይትድ ስቴትስ ተኩስ አቁምን ላልተወሰነ ጊዜ አራዘሙ

4/22/2026
የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ናፍጣ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ

Duration:00:04:06

Ask host to enable sharing for playback control

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ድረስ 47 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች መመዝገባቸውን አስታወቀ

4/21/2026
የኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምግብነት እየዋለ መሆኑ ተነገረ

Duration:00:05:36

Ask host to enable sharing for playback control

ዩናይድ ስቴትስ የኢራንን መርከብ በቁጥጥሯ ስር አዋለች፤ ኢራን የአፀፋ እርምጃ እወስዳለሁ አለች

4/20/2026
የዋን ኔሽን የሕዝብ አስተያየት ድጋፍ መውረድ ጀመረ፤ ሆኖም ከፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ ቀድሞ ሔዷል

Duration:00:04:25

Ask host to enable sharing for playback control

የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን "ቴዲ አፍሮ" ኢቶሪካ አልበም ሬኮርዶችን መስበሩን ቀጥሏል

4/20/2026
ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይቶች በሀገር ውስጥ ለመገጣጠምና መሞከር የሚያስችላትን ግዙፍ የማዕከል ግንባታ ከሩስያ የጠፈር ተቋም ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅቷን ማጠናቀቋ ተነገረ

Duration:00:11:00

Ask host to enable sharing for playback control

"የሴቶች ጉዳይ የተወሰኑ ሰዎች ኃላፊነት ብቻ አይደለም። ሁላችንም ለሴቶች ክብር፣ ነፃነት፣ እኩልነትና በዋናነት ለደህንነታቸው መቆም አለብን።" ናዲያ ሞናያ

4/17/2026
በሥርዓተ ትምህርት፣ የሴቶችና መድብለ ባሕል ተኮር የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ምርምራቸውን በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ እያካሔዱ ያሉት ወ/ት ናዲያ ሞናያ፤ ከፊል የምርምር ግኝቶቻቸውንና ፖሊሲ ነክ ጉዳዮችን አንስተው ያስረዳሉ።

Duration:00:10:26

Ask host to enable sharing for playback control

"ግጥም ውስጤ ያለውን ስሜት የምገልፅበት፣ አንባቢን በእኔ ዓለም ውስጥ፣ ስሜቶቼ ውስጥ የምጋብዝበት መድረክ ነው" ናዲያ ሞናያ

4/17/2026
በዩኒቨርሲቲ Exeter የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናዲያ ሞናያ፤ ምርምራቸው ስለሚያተኩርበት ለውጥ የሚያሻቸው የሴቶች ጉዳዮችና የመድብለ ባሕል ፋይዳዎችን አንስተው ያናገራሉ። ከግጥም ሥራዎቻቸው በቅርቡ "I Hugged a Tree" በሚል ርዕስ ለአባታቸው ዝክረ መታሰቢያ ከፃፉት የስንኝ ቋጠሯቸው በቅንጭቡ ያስደምጣሉ።

Duration:00:25:36

Ask host to enable sharing for playback control

"ከመማር ጋር ኃላፊነት አለ፤ የተማሩትን ለሌላው ማስተላለፍ የራስን ኃላፊነት መወጣት ነው። ለሕይወትም ትርጉም አለው።" ናዲያ ሞናያ

4/16/2026
ናዲያ ሞናያ - በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናቸው። ውልደትና ዕድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የኢትዮጵያዊት፣ ኤርትራዊትና ጣሊያናዊት ዝንቅ ብሔራዊ ማንነትን አጣምረው ይዘዋል። ሁለት ሀገርኛና አምስት የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ተናጋሪ ናቸው። የውልደት፣ ዕድገትና የትምህርት ሕይወታቸውን ነቅሰው ያጋራሉ።

Duration:00:19:00

Ask host to enable sharing for playback control

በአውስትራሊያ ጅሎንግ በሚገኝው የነዳጅ ማጣሪያ የእሳት አደጋ ተከሰት

4/16/2026
የአውስትራሊያ ከተሞች የራሳቸውን የነዳጅ ክምችት ለርመፍጠር ቅድመ ዝግጅት ጀምረናል አሉ

Duration:00:04:40

Ask host to enable sharing for playback control

Women’s legal services in Australia: Understanding your options - በአውስትራሊያ ለሴቶች ነጻ የህግ አገልግሎት ተቋማት አማራጮች እንዳሉ ይረዱ

4/15/2026
Workplace discrimination, gender-based violence and financial inequality—these are just some of the reasons why women need dedicated legal services. You don’t have to navigate the legal system alone. In Australia, free legal services exist to advocate for vulnerable women in ways that are safe, confidential and culturally appropriate. - ሴቶች የተለየ የህግ ባለሙያዎች እንዲያስፈልጋቸው ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል ፤ በስራ ቦታ የሚፈጸም መድልዎ ፤ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ፤ በገቢ ላይ የሚደረግ ማበላለጥ የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው ፡፡ በአውስትራሊያ የህግ ተቋማትን ብቻዎትን ማፈላልገ አይጠበቅብዎትም ፡፡ በችግር ላይ ያሉ ሴቶች ደህንነታቸ በተጠበቀ ሁኔታ ፤ ምስጢራቸው እና ባህላቸውን ባገናዘበ መልኩ ነጻ የህግ አገልግሎት አለ፡፡

Duration:00:10:29

Ask host to enable sharing for playback control

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ቀውስ በጦርነት አይፈታም ፤ መፍትሄው የሰላም ውይይት ነው - አንቶኒዮ ጉተሬዝ

4/15/2026
በሱዳን ከ 21 ሚልዮን በላይ ዜጎች ለጽኑ ረሀብ እና የምግብ እጦት ተጋልጠዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ወኪል አስታወቁ

Duration:00:07:32

Ask host to enable sharing for playback control

አገርኛ ሪፓርት - በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች መሰርታዊ አቅርቦት ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ገንዘብ ያስፈልጋል ተባለ

4/14/2026
በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ከደቡብ ሱዳን ፤ ኬንያ ኤርትራ እና ሶማሊያ የተፈናቀሉ ስደተኞች እንደሚኖሩ ተገለጸ

Duration:00:09:02

Ask host to enable sharing for playback control

በሺህ የሚቆጠሩ አራናውያን አሜሪካ በሆርሙዝ የጣለችውን ገደብ በቃወም ለሰልፍ ወጡ

4/13/2026
የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የኡበር አሽከርካሪዎች ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ ዋጋ እንዲያስከፍሉ ደንብ ወጣ

Duration:00:04:53