SBS Amharic-logo

SBS Amharic

SBS (Australia)

Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Location:

Sydney, NSW

Description:

Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Language:

Multilingual

Contact:

SBS Radio Sydney Locked Bag 028 Crows Nest NSW 1585 Australia (02) 9430 2828


Episodes

“በአፍሪካ ቀንድ ላይ የማተኮራችን ዓላማ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የእንግሊዝኛ ጽሑፍ መረጃ ክፍተትን ለመሸፈን ነው” - ሞገስ ከልክሌና ዮሴፍ አንተነህ

6/20/2021
አቶ ሞገስ ከልክሌ የHorn of Africa Insight ድረገጽ መሥራችና ዋና አዘጋጅ፤ አቶ ዮሴፍ አንተነህ የHorn of Africa Insight መሥራችና አባል፤ ስለ ድረገጻቸው ዋነኛ ተልዕኮ ያስረዳሉ።

Duration:00:12:23

ባለፈው አንድ አሠርት ዓመት የዓለም ስደተኞች ቁጥር በእጥፍ ናረ

6/19/2021
በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዓመታዊ ሪፖርት መሠረት፤ በዓለም ላይ በአስገዳጅ ሁኔታዎች ሳቢያ ለመፈናቀል ግድ የሚሰኙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሲሆን፤ ከቶውንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባይከሰትና ዓለም አቀፍ ድንበሮች ባይዘጉ ኖሮ የስደተኞች ቁጥር በእጅጉ የላቀ ይሆን እንደነበር ተመልክቷል።

Duration:00:05:15

ኒው ሳውዝ ዌይልስ በሕዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ላይ የፊት ጭምብል የማጥለቅ ገደብ ጣለች

6/18/2021
*** የአፍሪካ ኅብረት በትግራይ የተከሰተውን ቀውስ በተናጠል ምርመራ ለማድረግ መነሳቱ ያሳዘነው መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጠ

Duration:00:06:31

የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ በኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን አንደበት

6/18/2021
አቶ ጥላዬ ዱባለ (ከአደላይድ)፣ አቶ ዓለሙ ዘውዴ (ከፐርዝ)፣ አቶ ዮናስ መድፉ (ከሜልበርን) እና አቶ ሰይድ ዓሊ (ከብሪስበን)፤ የ2013 ብሔራዊ ምርጫን አስመልክቶ ግለ አተያያቸውን ያንጸባርቃሉ።

Duration:00:05:52

“አይጠየፍ አዳራሽ የወሎ አንድ የታሪክ ምዕራፍ ነው፤ ተገቢው ክብር ሊሰጠው ይገባል” ዶ/ር አሰፋ ባልቻ

6/17/2021
ዶ/ር አሰፋ ባልቻ፤ የቀድሞው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ናቸው። በቅርቡ በየሩብ ዓመት በሚታተመው Journal of Afroasiatic Languages, History andCultureላይ ለኅትመት ስላበቁት “Historic Ayteyefe Hall: An Imposing Artchitectural Piece in Dessie, Ethiopia” ጥናታዊ መጣጥፋቸው ይናገራሉ።

Duration:00:07:58

“የንጉሥ ሚካኤል የግብር አዳራሽ “አይጠየፍ” የተባለው የንጉሡ ሹመኞች፣ ካህናት፣ ድሆችና የአካል ጉዳተኞች ሁሉ ግብር ይበሉበት ስለነበር ነው” ዶ/ር አሰፋ ባልቻ

6/17/2021
ዶ/ር አሰፋ ባልቻ፤ የቀድሞው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ናቸው። በቅርቡ በየሩብ ዓመት በሚታተመው Journal of Afroasiatic Languages, History andCulture ላይ ለኅትመት ስላበቁት “Historic Ayteyefe Hall: An Imposing Artchitectural Piece in Dessie, Ethiopia” ጥናታዊ መጣጥፋቸው ይናገራሉ።

Duration:00:07:33

"ከሞትኩ በኋላ ሰው ላይ ክፋት የማይሠራ ሰው ብለው ቢያስቡኝ ይበቃኛል" - ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

6/15/2021
ጁን 10, 2021 ከዚህ ዓለም ለዘላለሙ ተሰናብተው ጁን 18, 2021 በአገረ አሜሪካ ቅዱስ ዮሐንስ ገዳም የሚያርፉት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ በቤተሰባቸው ልብ ውስጥ ማንም ሊሞላው የማይችለው ክፍተት መፍጠራቸው እውነት ነው። በሕይወት ሳሉ በተለይም ባለቤታቸውን ወ/ሮ ምሥራቅን ከሕይወታቸው ነጥለው አያዩ ስለነበር "ባለቤቴ ቆንጆ፣ ጨዋ፣ ለቤተሰብዋ ማንኛውንም ነገር አድርጋ መጨረሻ የምታገለግለው ራሷን ነው። ለኔ ሕይወቴ ነች" ብለው ነበር የሚገልጧቸው። እርግጥ ነው፤ ፕ/ር ጌታቸው በሥራዎቻቸውና የአገር ፍቅር ስሜታቸው ከሕይወት በኋላ ይኖራሉ።

Duration:00:13:58

የኢትዮጵያ የምረጡኝ ቅስቀሳ አበቃ

6/14/2021
*** አገርኛ ሪፖርት

Duration:00:07:22

"ሰዎች ሲሞቱ ከመቅበር ይልቅ በቁም እያሉ ማገዝ ይገባል" ቀድሰው ሁነኛው

6/13/2021
አቶ ቀድሰው ሁነኛው በሲድኒ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማኅበር ሰብሳቢ፤ የዕድሩ ዓላማና የ10 ዓመት እንቅስቃሴዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።

Duration:00:14:49

“ሃጫሉ የተወልን የአሻራ ዘር ከውስጣችን የማይፋቅ ነው” – ድምፃዊ ያደሳ ቦጂያ

6/13/2021
ያደሳ ቦጂያ - ግራፊክ ዲዛይነር፣ ድምፃዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋችና በመላው አፍሪካ በክብር የሚውለበለበው የአፍሪካ ኅብረት አርማ ዲዛይነር ነው። ሕይወቱ በሰው እጅ ለጠፋችው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ስላዘጋጀውና ጁን 20 ለሕዝብ ስለሚቀርበው የሙት ዓመት ዝክረ መታሰቢያ “ሃጫሉ” የሙዚቃ ሥራው ይናገራል።

Duration:00:09:07

ምርጫ 2013 “ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ እኩል የምትመች አገር እንድትሆን ያለንን ቁርጠኝነት ለሕዝብ ይዘን ቀርበናል ” – ቆንጂት ብርሃኑ

6/11/2021
ወ/ሮ ቆንጂት ብርሃኑ - የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) መሪ ናቸው። ፓርቲያቸውን በዘንድሮው የ2013 አገራዊ ምርጫ 103 ዕጩ የምክር ቤት አባላትን አሰልፏል። “ኢትዮጵያን ለማስቀጠል፣ በአገርነቷ እንድትቆይና ሉዓላዊነቷን እንድትጠብቅ ለማድረግ ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ ነው” ይላሉ።

Duration:00:08:34

ምርጫ 2013 - “ምረጥ ኢትዮጵያ” ለምን?

6/11/2021
አቶ ዘካርያስ ጌታቸው - የ “ምረጥ ኢትዮጵያ” ዘመቻ ዋና አስተባባሪ፤ ካፒቴን ዐቢይ ገብረሕይወት - የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ሊቀመንበርና የ “ምረጥ ኢትዮጵያ” ዘመቻ አስተባባሪ፤ የ2013ቱን አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክተው እያደረጉ ስላለው የባሕር ማዶ የምርጫ ዘመቻ እንቅስቃሴዎች ይናገራሉ።

Duration:00:12:40

በአውስትራሊያና ሲንጋፖር መካከል ከወሸባ ነፃ ጉዞ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ተደረሰ

6/11/2021
*** የኢትዮጵያ 2013 በጀት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጨማሪ 26.4 ቢሊየን ብር ፀደቀለት

Duration:00:06:43

የትግራይ ረሃብ ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግሥትና ተመድ ዓይኖች

6/11/2021
*** ግብፅና ሱዳን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሕዳሴን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት እንዲያስቆምላቸው እየጠየቁ ነው

Duration:00:08:23

በሜልበርን የኢትዮጵያውያን ምግብ ቤቶች የሁለት ሳምንታቱን የኮሮናቫይረስ ገደብ እንዴት ተወጡት?

6/11/2021
የአፍሪካ ኮቴጅ ምግብ ቤት ባለቤት ለማ ባልቻ፣ የኒያላ አፍሪካ ምግብ ቤት ባለቤት ኤርሚያስ ወንድሙና የጨርጨር ሬስቶራንት ባለቤት ፈትለወርቅ ግርማ፤ ለሁለት ሳምንታት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሜልበርን ላይ በተጣለው ገደብ የተንሳ በምግብ ቤቶቻቸው ላይ ስላደረሰው ተፅዕኖና እንደምን እየተቋቋሙት እንዳሉ ይናገራሉ። የገደቡ በዛሬው ዕለት መነሳት ያሳደረባቸውንም ተስፋ አክለው ይገልጣሉ።

Duration:00:04:11

“የዕምቦጭ አረምን ከ85 እስከ 90 ፐርሰንት ከጣና ሐይቅ ወደ ዳር ማስወጣት ተችሏል” - ዶ/ር አያሌው ወንዴ

6/10/2021
ዶ/ር አያሌው ወንዴ - የጣና ሐይቅና የሌሎች ውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የጣናን ሕልውና ስለፈተነው የዕንቦጭ አረም ምንጠራ ሂደትና ተደቅነው ስላሉ ስጋቶች ያነሳሉ። “በጣና ሐይቅ ላይ የተነጠፈውን አረም ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይዘዋወር ማድረግ ተችሏል። ይህ ማለት ግን ከሐይቁ ዳር አከማቸነው እንጂ አረሙ ሙሉ ለሙሉ ተወግዷል ማለት አይደለም። የአረሙ ክምችት ተጓጉዞ እንዲርቅ ለማድረግ የገንዘብ ችግር አለብን ” ይላሉ።

Duration:00:06:41

“እነ እስክንድር እሥር ቤት ሆነው ለምርጫ እንዲወዳደሩ በሕግ በመወሰኑ እንደ ፓርቲ ትልቅ አገራዊ ደስታ ነው የተሰማን” - ገለታው ዘለቀ

6/9/2021
አቶ ገለታው ዘለቀ - በዘንድሮው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ 23ቱም ክፍለ ከተሞችና በ137 የክልል ምክር ቤት ወንበር መወዳደሪያዎች ዕጩዎችን ያሰለፈው የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ ናቸው። “ከአገር በላይ ምንም ነገር የለም፤ ፓርቲም፣ ብሔርም የምንላቸው ነገሮች የሚስተናገዱት በአገር ጥላ ስር ነው። ፓርቲዎች ወደዚያ ከፍታ መምጣት አለባቸው” ይላሉ።

Duration:00:10:53

“አማርኛ የመሞት ሥጋት የለበትም፤ እንግሊዝኛ ወደ ወጣቶቻችን ዓረብኛ ወደ ልጆቻችን ሥርዓቱን ባልጠበቀ መንገድ እየደረሱ ነው” ፕ/ር ዘላለም ልታየው

6/8/2021
ፕሮፌሰር ዘላለም ልታየው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልሳን መምህር፤ በቅርቡ በየሩብ ዓመት በሚታተመው Journal of Afroasiatic Languages, History andCulture ላይ ለኅትመት ስላበቁት “Notes on language change in Amharic” ጥናታዊ መጣጥፋቸው ይናገራሉ። “የአማርኛ ቋንቋ ያልተለመደ ዕድገት ላይ ሃይ ባይ ጠፋ” ይላሉ።

Duration:00:15:00